top of page

የፆም ፓንኬክ 🥞

  • Foto del escritor: Beti Fitness
    Beti Fitness
  • 24 mar 2019
  • 1 Min. de lectura

ከከባድ እንቅስቃሴ በሗላ ሁሌም የምያምረኝ ነገር ቢኖር ካርቦሃይድሬት ነክ ምግብ ነው:: ከጤነኛ የምግብ ምንጭ ሲመጣ ካርቦሃይድሬት ለሰውነታችን ጠቃሚና ሀይል ሰጪ ንጥረ ነገር ነው::

ይሄንን ፓንኬክ ስፈላሰፍ ሰርቼው እንደቀመስኩት ነው የወደድኩት 😂:: በካርቦሃይድሬትም በፕሮቲን የተሟላ ነው::



1 ማንኪያ ቀረፉ (ወይንም 1 ማንክያ ካካው ፓውደር)

1/4 ኩባያ የኣጃ ዱቄት (ወይንም ኣጃ ተፈጭቶ)

1/4 ኩባያ የሽምብራ ዱቄት

1/2 ማንክያ ቤኪንግ ሶዳ


1 ሙዝ

1/2 ኩባያ ሶይ ወይንም አልመንድ ወይንም የላም ወተት

1 ማንክያ የኦቾሎኒ ቅቤ

1/2 ማንክያ ኮኮናት ቅቤ

1/2 ማንክያ የተፈጨ ተልባ


1. ደረቅ ምግቦቹን በሰሀን ማደባለቅ(ቀረፋ: ዱቄት: ቤኪንግ ሶዳ )


2. ሙዙን: የኦቾሎኒና የኮኮናት ቅቤውን: ወተቱንና ተልባውን መፍጨት


3. ደረቅና እርጥብ ምግቦቹን ማወሃድ


4. ሊጡን በጋለ መጥበሻ ለይ እንደ ቂጣ መጋገር


ከፍራፍሬ: ቅቤ: ወይንም ማር ጋ አድርጎ ማቅረብ ይቻላል!



English version: https://betifitness.wixsite.com/blog/blog/vegan-pancakes


Comentarios


Post: Blog2_Post

Subscribe Form

Thanks for submitting!

  • Instagram
  • YouTube

©2018 by Beti Fitness. Proudly created with Wix.com

bottom of page