top of page

አተር ክክ ከሪ | Split Pea Curry

Actualizado: 15 ene 2021

አተር ክክ ከሪ አዘገጃጀት

ከሪ ወጥን የመሰለ በቅመም የሚሰራ ህንዳዊ የምግብ አዘገጃጀት ነው:: ይሄ በጣም ከምወደው የከሪ አሰራር አንዱ ነው:: አጥጋቢ ጣፋጭና በጤነኛ አትክልትና ፕሮቲን የተሟላ በመሆኑ አራኪና የሚያሞቅ ምግብ ነው::



የምያስፈልገው

1 እስከ 2 ኩባያ አተር ክክ

1 ወይም 2 ቲማቲም

2 እፍኝ ጎመን (ወይንም ሌላ አረንጓዴ ቅጠል)

400ml ወተት ወይም 1 ጣሳ የኮኮናት ወተት


ለመቀመመያ

1 ሽንኩርት

የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት

የተፈጨ ዝንጅብል

በርበሬ

ዕርድ

ጨው

ቁንዶ በርበሬ


አሰራሩ

  1. ክኩን ከ2-3 ኩባያ ውሃ ጋ በትልቅ ድስት ለ30-45 ደቂቃ መጣድ::

  2. ክኩ እየበሰለ ሽንኩርቱን አድቅቆ ከትፎ ከዘይት ጋር ማቁላላት:: 1 የሻይ ማንክያ ነጭ ሽንኩርት: ዝንጅብል: በርበሬ: ዕርድ: ጨውና: ቁንዶ በርበሬ መጨመር::

  3. ሽንኩርቱ ሲለሰልስ ቲማቲም ከትፎ መጨመር:: ለ 15-20 ደቂቃ ማብሰል::ቀጥሎ ስልሱን ክክ ውስጥ ጨምሮ ማደባለቅ::

  4. ክኩ መብሰሉን ማረጋገጥ፤ ካስፈለገ ተጨማሪ ውሃ መከለስ:: ክኩ ሲቀመስ ዉሃውን መጠጥ አድርጎ ግን ለስለስ ያለና ያልደረቀ መሆን አለበት:: ከደረሰ ወተቱንም መደባለቅ::

  5. ጎመኑን አድቆ ከትፎ መጨመር:: ለ10-15 ደቂቃ ከሪዉን ማንተክተክ::

ከሩዝ ወይንም ቂጣ ጋ ማቅረብ ይቻላል:: ለብቻውንም ቢበላ ይጥማል::

አማራጭ:- ማንኛውም አይነት ወተት መጠቀም ይቻላል:: ይላም ወተትና የኮኮናት ወይንም ካሽው ወተት ወፈር ያደርገዋል: ሌላ የጾም ወተት አይነት ያቀጥናል::

 

Curry Recipe

This is one of my favorite curry recipes - perfect for dinner. Satiating, flavorful and packed with wholesome veggies and protein to keep you full and warm.



What you will need:

1-2 cups split peas

1-2 tomatoes

1 can of coconut milk

2 handfuls of leafy greens (usually kale or spinach)


to season:

1 onion

crushed garlic

crushed ginger

cumin or curry powder

berbere or ground chilli pepper

salt and pepper


Recipe:

  1. Pour the split peas and 2-3 cups of water in a large pan and let cook for 30-45 minutes.

  2. As the peas cook, dice the onion and heat with oil in a wider pan. Season with a teaspoon each of garlic, ginger, cumin, berbere, salt and pepper.

  3. Once the onion is soft, add the tomatoes, diced. Let cook for 15-20 minutes and then pour all the contents of the pan into the split peas.

  4. Check to see if the peas need more water or time. They should be soft to taste and although they will soak up the water, they shouldn't be completely dry. Once they are soft, add the coconut milk.

  5. Dice the kale or spinach (or add directly if frozen) and add it to the pan. Allow everything to simmer for about 10 minutes more.

Serve with rice, naan or by half the curry by itself! Tastes great either way.


Optional: You can also use regular milk, cashew milk, oat milk. Other types of milk usually tends to be a bit runnier but will work too.


Commentaires


Post: Blog2_Post
bottom of page