የጾም በርገር አሰራር
- Beti Fitness
- 27 dic 2018
- 1 Min. de lectura
6-10 በርገር ይሰራል

የምያስፈልጉ ምግቦች
1½ ኩባያ ምስር (ተቀቅሎ)
1 ሽንኩርት (በደቃቁ ተከትፎ)
2 ፍርቃጭ ነጭ ሽንኩርት (ከዝንጅብል ጋ ወይንም ለብቻውን ደቆ)
1 ኩባያ እንጉዳይ ወይንም ቴስቲ ሶያ (ደቆ)
1 ኩባያ አጃ
1 የሾርባ ማንክያ ተልባ
3 ድንች
የወይራ ዘይት (ለማብሰያ)

ቅመሞች:
ጨው
ቁንዶ በርበሬ
ከሙን
እርድ
በርበሬ
የስጋ መጥበሻ (ደርቆ የተፈጨ)
ለማቅረብያ ዳቦ: ቲማቲምና ሰላጣ
የበርገሩ አዘገጃጀት
1. ቺፕስ ለመስራት መጋገርያውን ለኩሶ ማሞቅ::
2. ተልባውን ከ2 የሾርባ ማንክያ ውሀ ጋር ቀላቅሎ ማስቀመጥ::
3. ትንሽ ዘይት (ወደ አንድ የሾርባ ማንክያ) መጥበሻ ላይ አድርጎ ከጋለ በኅላ ሽንኩርቱን ማቁላላት::
4. ነጭ ሽንኩርት: ጨው: ቁንዶ በርበሬና እርድ (አንድ አንድ የሻይ ማንክያ) ጨምሮ ሽንኩርቱ ቀለም እስኪለውጥ ለ5 ደቂቃ የሀል ማብሰል::
5. ከእሳት ላይ አንስቶ በሰሀን ላይ ሽንኩርቱን ማቀዝቀዝ::
6. ሽንኩርቱ የነበረበት መጥበሻ ላይ ሌላ የሾርባ ማንክያ ዘይት አግሎ እንጉዳዩን (ወይንም ቴስቲ ሶያውን) ለ10 ደቂቃ ማብሰል:: ከ3ደቂቃ በኅላ በርበሬውን መጨመር::
7. በምግብ መፍጫ ውስጥ: ሽንኩርቱን: ምስሩን: ተልባውንና አጃውን ጨምሮ መፍጨት::
8. ከመፍጫ አውጥቶ በትልቅ ሰሀን ቅልቅሉን ከበሰለው እንጉዳይ ወይንም ሶያ ጋር በእጅ ማዋሀድ::
9. ክብ ቅርጽ እያድቦለቦሉ በመጠፍጠፍ የበርገር ቅርጽ መስራት::
10. በርገሮቹን ለ20 ደቂቃ እስከ ግማሽ ሰዓት በረዶ ቤት ውስጥ ማቆየት::የምያስፈልገውን ያህል አውጥቶ በትንሽ ዘይት መጥበስ:: የቀሩትን በረዶ ቤት በምሳቃ ወይንም ziplock ማስቀመጥ:: ከተጠበሱ በኅላ ዳቦ መሀል ከቶ ከሰላጣና ከቲማቲም ጋር ማቅረብ::
የቺፕሱ አዘገጃጀት
1. ድንቹን አጥቦ በረዥሙ መክተፍ::
2. በሰሀን ውስጥ ከአንድ ወይንም ሁለት የሾርባ ማንክያ ዘይት: ጨው: ቁንዶ በርበሬና ስጋ መጥበሻ ጋር መቀላቀል::
3. በዘይት ወይንም aluminum foil በተሸፈነ ፓትራ ላይ አርጎ ለ15 ደቂቃ መጋገር::
4. ድንቹ በአንዱ በኩል ከበሰለ በኅላ ከመጋገርያው ፓትራውን አውጥቶ ድንቾቹን በመገልበጥ መልሶ ከቶ ለ15 ደቂቃ ማብሰል::

አንድ ላይ ከኬቻፕ ጋር ማቅረብ::

Comments